አቻ አልተገኘልህም
Acha Altegegnelehem
2009 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁሉም ያበጀውን አምላኩን ሲጠራ
የአማልክቱን ሥም በተራ በተራ
አንድ ጊዜ ብቻ አቤቱ ስለዉ
እሳት ሆኖ መጣ አቻ የሌለዉ
አዝማች · Chorus
አቻ አቻ የሌለው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አላየንም ሌላ አላየንም
ሚሾም ሚሽር የለው ሥልጣኑን
አላየንም ሌላ አላየንም
አጋዥ አጋር የለው መንግስቱን (፪x)
አዝማች · Chorus
አቻ አቻ የሌለው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
(አሃ አሃሃ) ሁሌ እርሱ ሌላ አይሻ
(አሃ አሃሃ) አልፋ ነው መጨረሻ
(አሃ አሃሃ) የዕውቀት ራስ የጽድቅ ጫፍ
(አሃ አሃሃ) ይኖራል ስንቱ ሲያልፍ
(አሃ አሃሃ) በዕድሜው አንድ ቀን
(አሃ አሃሃ) ሲሸነፍ አላየንም
(አሃ አሃሃ) ፎክረው ሲጨርሱ
(አሃ አሃሃ) ያኔ ነው እርሱ መልሱ
ቁጥር 4 · Verse 4
አቻ አልተገኘልህም ወደር አልተገኘልህም (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ቀዳማዊ እርሱ ነው የሁሉም ፊተኛ
ግርማዊም እርሱ ነው ስልጣኑ ብቸኛ
በቤተ-መንግስቱ በዙፋኑ ላይ
ሌላው ዝቅ ብሎ እርሱ ከብሮ ይታይ
ቁጥር 6 · Verse 6
ይታይ እርሱ ከብር ይታይ (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
አላየንም ሌላ አለየንም (አላየንም)
ሚሾም ሚሽር የለው ስልጣኑን (ሥልጣኑን)
አላየንም ሌላ አለየንም (አላየንም)
አጋዥ አጋር የለው መንግስቱን (መንግስቱን)
አዝማች · Chorus
አቻ አቻ የሌለው (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ