ላመስግነው
Lamesgenew
2009 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዙሪያዬን ሳይ ለመዳኔ ሰው የለኝም አንድ ለእኔ
ሰድበኸው ሙት አትበሉኝ ለእኔው ጥቅም ሲፈትነኝ
ሁሉ እያለ ከእኔ ጋራ አፌ ከንቱ መቼ አወራ
ለማመስገን ለውዳሴ ይበቃኛል እስትንፋሴ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው ሲጠበቅ እንባዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ለቅሶዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰጠውን ጌታ ቢነሳ ስላለው ነው ያን የሚያስረሳ
ሊያልፍ ነገር አላማርርም ምሥጋናዬን አላጓድልም
የሰጠውን ጌታ ቢወስደው ስላለው ነው ያን የሚበልጠው
ሊያልፍ ነገር አላማርርም ምሥጋናዬን አላጓድልም
ላመስግነው ቢጐድልም ቢሞላ ላመስግነው አምላክ የለኝ ሌላ
ላመስግነው ዛሬ ያለኝ ቢነሳ ላመስግነው ትላንትን አልረሳ
ላመስግነው ቢጐድልም ቢሞላ ላመስግነው አምላክ የለኝ ሌላ
ላመስግነው እምነቴ ቢለካ ላመስግነው ለበጐ ነው ለካ
ከባርነት ሲያሻግረኝ ጠላቶቼን ሲጥልልኝ
ከበሮ ይዤ እንደዘመርኩ ተዓምራቱን እንደተረኩ
ዛሬም ሳልፍ በበረሃው አንደኛ ነኝ ለምሥጋናው
እየታየኝ ከፊት ተስፋ ላመስግነው ከምከፋ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው ሲጠበቅ እንባዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ለቅሶዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ላመስግነው ቢጐድልም ቢሞላ ላመስግነው አምላክ የለኝ ሌላ
ላመስግነው ዛሬ ያለኝ ቢነሳ ላመስግነው ትላንትን አልረሳ
ላመስግነው ቢጐድልም ቢሞላ ላመስግነው አምላክ የለኝ ሌላ
ላመስግነው እምነቴ ቢለካ ላመስግነው ለበጐ ነው ለካ
ዙሪያዬን ሳይ ለመዳኔ ሰው የለኝም አንድ ለእኔ
ሰድበኸው ሙት አትበሉኝ ለእኔው ጥቅም ሲፈትነኝ
ሁሉ እያለ ከእኔ ጋራ አፌ ከንቱ መቼ አወራ
ለማመስገን ለውዳሴ ይበቃኛል እስትንፋሴ
አዝማች · Chorus
ላመስግነው ሲጠበቅ እንባዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ለቅሶዬ ላመስግነው
ላመስግነው ሲጠበቅ ሀዘኔ ላመስግነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ