ልበልህ አለኝታዬ
Lebeleh Alegntayie
2009 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የሞትክልኝ በእኔ ቦታ
አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የቆምክልኝ በእኔ ቦታ
(ኧኸ) ጅማሬዬ ላይ (ኧኸ) ታሪክ ሲዘጉ
(ኧኸ) ቁጣህ ነደደ (ኧኸ) አንተን እንደነኩ
(ኧኸ) ወጪ ወራጁ (ኧኸ) የሚቀናበት
(ኧኸ) ክብርህ ፈሰሰ (ኧኸ) ገባ ከእኔ ቤት
አዝማች · Chorus
ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ)
ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
(ኧኸ) ሲማማምሉና (ኧኸ) ሲማከሩብኝ
(ኧኸ) ፍላጻህ ወርዶ (ኧኸ) አፈረሰልኝ
(ኧኸ) በጠላት ቀዬ (ኧኸ) በጠላት መንደር
(ኧኸ) ስለአለኝታዬ (ኧኸ) እስኪ ልዘምር
አዝማች · Chorus
ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ)
ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላቴ ብዙ ለፍቶ በእጁ ሊያስገባኝ ጓግቶ
ፍቅርህ ያሰረው ልቤ አንተን አለኝ ሀሳቤ (፪x)
አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የሞትክልኝ በእኔ ቦታ
አምላኬ ሆይ የእኔ አለኝታ የቆምክልኝ በእኔ ቦታ
(ኧኸ) ማለዳ ቀትር (ኧኸ) ነግቶ እስኪመሽ
(ኧኸ) በእኔ ዝማሬ (ኧኸ) ጠላት ሲረበሽ
(ኧኸ) የማታው ለቅሶ (ኧኸ) ጠዋት ደስታ
(ኧኸ) እንዲህ ነው እንጂ (ኧኸ) ማረፍ በጌታ
አዝማች · Chorus
ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ)
ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጥቃቴን ከላይ አይተህ ክብርህን ለእኔ ትተህ
ወርደህ ያወጣኸኝ ሞተህ ያተረፍከኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ልበልህ (ልበልህ) አለኝታዬ (አለኝታዬ)
ልበልህ (ልበልህ) ከለላዬ (ከለላዬ) (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ