አየልኛ
Ayelegna
2009 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያረገልኝ እንዴት ይረሳል
አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ብዙ ብዙ
ፍቅሩ ብዙ ብዙ
ሰላሙ ብዙ ብዙ
ምህረቱ ብዙ ብዙ
ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (፬x)
መች እዘገናለሁ የትላንቱን
አስታውሰዋለሁ እያንዳንዱን (፪x)
እኔ ነኝ የማውቀው እኔ ነኛ
ከጐኔ ሰው ሳይኖር ወይ ጓደኛ
እኔ ነኝ የማውቀው እኔ ነኛ
የዛሬው ከፍታ ታየልኛ (፪x)
አዝማች · Chorus
አየልኛ ብዙ መልካም
ቁጥር 2 · Verse 2
አየልኛ ለኔው ሰላም
አየልኛ ብዙ እረፍት
አየልኛ የማልፍበት (፪x)
ያረገልኝ እንዴት ይረሳል
አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ብዙ ብዙ
ፍቅሩ ብዙ ብዙ
ሰላሙ ብዙ ብዙ
ምህረቱ ብዙ ብዙ
ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (፬x)
ያ ታሪኬ ዛሬ ተቀይሮ
ሰው አይቶም አያውቀኝ አብሮኝ ኖሮ
ያ ታሪኬ ዛሬ ተቀይሮ
የቅርብ አይለየኝ አብሮኝ ኖሮ
አትፈልጉ ሌላ እኔ ነኝ
በምህረቱ ብቻ የቆምኩኝ
አትፈልጉ ሌላ ራሴ ነኛ
እንዲሁ በፀጋው ወደደኛ (፪x)
ወደደኛ ያኔ ድሮ
ወደደኛ ሌላው ዞሮ
ወደደኛ ሳይቀየር
ወደደኛ በዛው ፍቅር (፪x)
ያረገልኝ እንዴት ይረሳል
አበቃ ስል ጌታ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ብዙ ብዙ
ፍቅሩ ብዙ ብዙ
ሰላሙ ብዙ ብዙ
ምህረቱ ብዙ ብዙ
ጌታ አለብኝ ያንተ ውለታ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ