እኔ አላየሁም
Enie Alayehum
2009 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ልቤ ያመነብህ ውስጤ ያረፈብህ
የሕይወቴ ዋልታ ሁሉን የጣልኩብህ
ልቤ ያመነብህ ውስጤ ያረፈብህ
የቤቴን ምሰሶ ሁሉን የጣልኩብህ
እኔ አላየሁም አንተን መሳይ
እኔ አላየሁም ውስጤን የሚያይ
እኔ አላየሁም ማን አለኝና
እኔ አላየሁም ፍቅሩ የፀና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ልዩ ነው ፍቅርህ (፪x)
ልዩ ነው መውደድህ (፪x)
ምኔን አይቶ ነው ምን ተገኝቶብኝ
ከሰዉ መሃል ዓይኑ ያረፈብኝ
ለፍቅር ብሎ ያልሆነው የለም
በባዶ የሚወድ እኔ አላየሁም
እኔ አላየሁም አንተን መሳይ
እኔ አላየሁም ውስጤን የሚያይ
እኔ አላየሁም ማን አለኝና
እኔ አላየሁም ፍቅሩ የፀና (፪x)
ልዩ ነው ፍቅርህ (፪x)
ልዩ ነው መውደድህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ አላየሁም ሞቶ ሚታደግ
እኔ አላየሁም ሕያው የሚያደር
እኔ አላየሁም በነፍሱ ቤዛ
እኔ አላየሁም ሁሉን የገዛ
እኔ አላየሁም ዘሬም አልሰማ
እኔ አላየሁም ኧረ እንዳንተማ
እኔ አላየሁም ለሁሉ አሳቢ
እኔ አላየሁም ፍቅሩ ሰፊ
አዝማች · Chorus
ልቤ ያመነብህ ውስጤ ያረፈብህ
የሕይወቴ ዋልታ ሁሉን የጣልኩብህ
ልቤ ያመነብህ ውስጤ ያረፈብህ
የቤቴን ምሰሶ ሁሉን የጣልኩብህ
እኔ አላየሁም አንተን መሳይ
እኔ አላየሁም ውስጤን የሚያይ
እኔ አላየሁም ማን አለኝና
እኔ አላየሁም ፍቅሩ የፀና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የዛሬውን እንጂ የነገው
ማን ያውቃል ምን እንደሚያረገው
ትላንትን ሳስበው አመንኩት
አሳልፌ በእጁ ሰጠሁት (፪x)
ልቤን በፍቅርህ ነፍሴን በምክርህ
የምታረካ አንተ ብቻ ነህ
ሚስጥረኛዬ የልቤ የምለው
እኔን የሚያውቀኝ እንዳንተ ማነው
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔ አላየሁም አንተን መሳይ
እኔ አላየሁም ውስጤን የሚያይ
እኔ አላየሁም ማን አለኝና
እኔ አላየሁም ፍቅሩ የፀና (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ