ትቼልሃለሁ
Techielehalehu
2009 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ግራ ሲገባኝ ሌላን አይቼ
እርፍ እላለሁ ለአንተ ሰጥቼ
ግራ ሲገባኝ ሁኔታ አይቼ
እርፍ እላለሁ በአንተ ላይ ትቼ
አዝማች · Chorus
ትቼልሃለሁ ጌታዬ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ከእንግዲህ ትቼልሃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በአንተ ላይ ነገሬን ትቼ
በአንተ ላይ አምኜ ወጥቼ
በአንተ ላይ አፍሬ አላውቅም
በአንተ ላይ በአንተ ኮርቼ (፪x)
አይጥልማ አይረሳማ የእኔ ጌታ
አልናወጥ በሚሰማ በሁኔታ (፪x)
ከንጉሥ ተስፋ ከአለቆች ቃል
ነፍስ መንፈሴ አንተን አምኖሃል
ባያምኑህ እንኳን ታምነህ የምትኖር
ትቼልሃለሁ ጌታ የእኔን ነገር (፪x)
አዝማች · Chorus
ትቼልሃለሁ ጌታዬ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ከእንግዲህ ትቼልሃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ግራ ሲገባኝ ሌላን አይቼ
እርፍ እላለሁ ለአንተ ሰጥቼ
ግራ ሲገባኝ ሁኔታ አይቼ
እርፍ እላለሁ በአንተ ላይ ትቼ
አዝማች · Chorus
ትቼልሃለሁ ጌታዬ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ከእንግዲህ ትቼልሃለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የተናገረኝ ያየልኝ ያኔ
ይሆናል አመንኩ ሳላየው በዓይኔ
ገመዴ ወድቃ ባማረ ስልፍራ
አልገባም እኔስ በአምላኬ ስራ (፪x)
አይጥልማ አይረሳማ የእኔ ጌታ
አልናወጥ በሚሰማ በሁኔታ (፪x)
በአንተ ላይ ነገሬን ትቼ በአንተ ላይ አምኜ ወጥቼ
በአንተ ላይ አፍሬ አላውቅም በአንተ ላይ በአንተ ኮርቼ
ነገሬን ነገሬን ትቼ አምኜ አምኜ ወጥቼ
አፍሬ አፍሬ አላውቅም በአንተማ በአንተ ኮርቼ
አይጥልማ አይረሳማ የእኔ ጌታ
አልናወጥ በሚሰማ በሁኔታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትቼልሃለሁ ጌታዬ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ከእንግዲህ ትቼልሃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ