አትለዋወጥም
Atelewawetem
2009 · ትራክ 12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዓመቱ የታለ ወራትና ቀኑ
እርግጥ አይኖርም ክፉ ነው ዘመኑ
አንተማ ዛሬም ያው ትላንት እንደ አዩህ
ስትለውጥ እንጂ ተለውጠህ አያውቁህ (፬x)
አዝማች · Chorus
(አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም
(አንተማ) አትቀያየርም
(አንተማ) መቼ እንደሰዉ
(አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢየሱሴ መድኃኒት ለነፍሴ
ኢየሱሴ ማምለጫ ለነፍሴ (፪x)
ወዳጅ ወዳጅ ወዳጅ እንዳለው ሰዉ
እኔም ካንተ ጋራ እወዳጃለሁ
አምላክ አምላክ አምላክ እንዳለው ሰዉ
እኔም ከአንተ ጋራ መኖር እሻለሁ
አዝማች · Chorus
(አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም
(አንተማ) አትቀያየርም
(አንተማ) መቼ እንደሰዉ
(አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱሴ መድኃኒት ለነፍሴ
ኢየሱሴ ማምለጫ ለነፍሴ (፪x)
ብትወደኝ እኮ ነው ይኸው እስከዛሬ
በፍቅርህ ታስሬ አብሬ መኖሬ
አመል ሆኖብኛል አንተን አንተን ማለት
ወዳጅ ስትሆነኝ ወረት የሌለበት (፬x)
አዝማች · Chorus
(አንተማ አንተማ) አትለዋወጥም
(አንተማ) አትቀያየርም
(አንተማ) መቼ እንደሰዉ
(አንተማ) ፍቅርህ ልዩ ነዉ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱሴ ጠበቃ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ዋስትና ለነፍሴ
ኢየሱሴ አለኝታ ለነፍሴ
ኢየሱሴ መከታ ለነፍሴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ