Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አቻ አልተገኘልህም

Title

2009 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳመልክህ እንድኖር ውስጤ ሳይል ዝም

ምነው ቀኑ ባይኖር ሌቱም ባይጨልም

መንፈሱን ፈልጌ ተዘልዬ እኔማ

ሰከንዷም አትለፍ ድምጼ ሳይሰማ (፪x)

እኔማ እንዴት ችዬ ዝም

እኔማ አምልኮዬ አይቆም (፪x)

ጌታዬ መጣና እንባዬን አየና

ነገሬን ፈወሰው የልቤ ደርሰ

አይደለም ከሩቅ አለሁ ባዬ

እንዲህ ነው ሲሰራ ጌታዬ (፪x)

እንዳሰብኩት ባይሆን (ይሁና አዋቂ ነውና)

የልቤ ባይሞላ (ይሁና አዋቂ ነውና)

መልሴ ቢዘገይም (ይሁና አዋቂ ነውና)

ቅትር ላይ ቢጨልም (ይሁና አዋቂ ነውና)

ምክንያቴን ጥዬ ሰበቤን ትቼ

አመልካለሁኝ አምላክ አግኝቼ (፪x)

ሳመልክህ እንድኖር ውስጤ ሳይል ዝም

ምነው ቀኑ ባይኖር ሌቱም ባይጨልም

መንፈሱን ፈልጌ ተዘልዬ እኔማ

ሰከንዷም አትለፍ ድምጼ ሳይሰማ (፪x)

እኔማ እንዴት ችዬ ዝም

እኔማ አምልኮዬ አይቆም (፪x)

እረስቶታል አሉ (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ)

አባትነቱ የታል (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ)

ህልሜን ህልም ቢሉት (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ)

ሆኖ እስከሚያዩት (ይበሉ ይፈጸማል ቃሉ)

ምክንያቴን ጥዬ ሰበቤን ትቼ

አመልካለሁኝ አምላክ አግኝቼ (፪x)

ኢየሱሴ መጣና እንባዬን አየና

ነገሬን ፈወሰው የልቤ ደርሰ

አይደለም ከሩቅ አለሁ ባዬ

እንዲህ ነው ሲሰራ ጌታዬ (፪x)

እኔማ እንዴት ችዬ ዝም

እኔማ አምልኮዬ አይቆም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ