Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አዲስ ሰው

Adis Sew

2016 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በክርስቷስ አዲስ ሰዉ ነኝ አዲስ ፍጥረት ኃጥያት ማይገዛኝ

ነፃ ሆንኮኝ ከኩነኔ በእርሱ ስራ አምኜ አዲስ ሰዉ ነኝ

አዲስ ፍጥረት የሌለብን ኃጥያት ሞት

በመስቀሉ አምኛለሁ በእርሱ ፀድቂለሁ

ከጨለማ አዉጥቶ በብርኃን ሊመራኝ

በእምነት አፀደቀኝ የራሱ አረገኝ

በክርስቶስ ስራ በመስቀሉ ሚስጥር

በማሜኔ ብቻ ዳግም ተወለድኩኝ

አዲስ ፍጥረት የሌለብን ኃጥያት ሞት

በመስቀሉ አምኛለሁ በእርሱ ፀድቂለሁ

በነፃነት ልኖር ነፃ አዉጥቶኛል

አልሰጋም ከእንጊዲህ ቃሉ ይመራኛል

ፃድቅን እንደ አንበሳ ያለ ፍርኃት ይኖራል

ይህ ነዉ ማንነቴ እዉነቱ ገብቶኛል

አዲስ ፍጥረት የሌለብን ኃጥያት ሞት

በመስቀሉ አምኛለሁ በእርሱ ፀድቂለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ