ልቅረብህ
Leqrebeh
2016 · ትራክ 7 · 6:30 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዋላ ወደ ዉሃ ምንጭ እንደምትናፍቅ
ነፍሴን አንተን ተጠማች
አንተን ትናፍቅሐለች
አቅሜ ነህና ብርታቴ ነህና
ሁሌም ልቅረብህ ጌታ ፊትህ ልምጣና
አዝማች · Chorus
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ካንተ ጋር የዋለ ክብርሕንም ያየ
መች ሌላ ነገር ያሰኘዋል ሁልጊዜ ይናፊቅኃል
ክብር አለዉ ፊትህ ግርማ ሞገስህ
ይፈሩኃል ያከብሩኃል አንተን ሚወዱ
አዝማች · Chorus
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ልቅረብህ አብዝቼ ልወቅህ አብዝቼ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ያወኩ ለታ ወድሀለሁ ፈራሀለሁ እመስልኃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የእምነት አባቶቼ ለጽድቅ የጨከኑ
ላንተ ለመኖር ብቻ የወሰኑ
ወንጌሉን የእዉነት ያመኑ
ምድርን የናቁ ከኃጥያት የራቁ
ምሳሌ ሆነዉ አልፈዋል አንተን ያወቁ
ፊትህ ልምጣ ልፈልግህ ሰላሜ ያለዉ እግር ስር
ፊትህ ልምጣ ልፈልግህ ደስታዬ ያለዉ እግር ስር
ፊትህ ልምጣ ልፈልግህ ሰላሜ ያለዉ እግር ስር
ፊትህ ልምጣ ልፈልግህ ደስታዬ ያለዉ እግር ስር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ