ልጁ ነኝ
Leju Negn
2016 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በኃጥያቴ በበደሌ ሙት የነበርኩ እኔ
አስቀድሞ ነበረብኝ ፍርድና ኩኔኔ
አሁን በመስቀሉ ስራ ዋጋ ተከፍሎልኝ
በክርስቶስ ተወደድኩኝ ልጁ ተደረኩኝ
አዝማች · Chorus
ልጁ ነኝ የሚወደኝ ሚረዳኝ ሚደግፈኝ
አልሄደም ካጠገቤ ፍቅር ነዉ ሁሌ ለእኔ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለሰዉ ፍቅር ለመዋደድ ምክንያት ይፈልጋል
ዛሬ ወዶት ነገ ሲያድርጠላቱ ይሆናል
ማይለወጥ ማይቀየር ንፅህ ፍቅር ያለዉ
እዉነተኛ አባቴ ነዉ ፍቅር እየሱስ ነዉ
አዝማች · Chorus
ልጁ ነኝ የሚወደኝ ሚረዳኝ ሚደግፈኝ
አልሄደም ካጠገቤ ፍቅር ነዉ ሁሌ ለእኔ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኦኦ…..ኦኦኦ…..ኦኦኦኦኦ……ልጁ
ነኝ…….ልጁ ነኝ……ልጁ ነኝ…….ልጁ ነኝ
አቅም ሳጣ ሲያዝል ልቤ እምነቴ ሲደክም
የቀደመዉ ፍቅሬ ጠፍቶ ዉስጤ ሲፍገመገም
አይኔን ወደ እርሱ ሳነሳ በፍቅር እያየኝ
እጄን ይዞ አበረታኝ እንደገና አቆመኝ
አዝማች · Chorus
ልጁ ነኝ የሚወደኝ ሚረዳኝ ሚደግፈኝ
አልሄደም ካጠገቤ ፍቅር ነዉ ሁሌ ለእኔ
ቁጥር 4 · Verse 4
ኦኦ…..ኦኦኦ…..ልጁ ነኝ………ኦኦኦኦኦ……ልጁ
ነኝ…….ኦኦኦኦኦኦ………ልጁ ነኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ