Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ባወዳድስህ

Bawedadeseh

2016 · ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባወዳድስ ባሞጋግስህ ዝምብዬ አይደል አለኝ ምክንያት

ሁሌ ይደንቀኛል ፍቅሩ ምሕረቱ ፍጥረት ይዘምር ይስገድ በፊቱ

ኃጥያተኛ ነሽ ብለዉ ፈረጁ

ድንጋይ አነሱ ወግረዉ ሊገድሉኝ

ፈራጁ እየሱስ ፈረደልኝ

ደግመሽ አትስሪ ሂጅ አለኝ

ለተመለሰ ያለፈዉን ትቶ

ፍርዱ ፍቅር ነዉ ያነሳል መልሶ

ለተመለሰ ያለፈዉን ትቶ

ፍርዱ ፍቅር ነዉ ያነሳል መልሶ

ባወዳድስ ባሞጋግስህ ዝምብዬ አይደል አለኝ ምክንያት

ሁሌ ይደንቀኛል ፍቅሩ ምሕረቱ ፍጥረት ይዘምር ይስገድ በፊቱ

ከቤቱ ጠፋዉ ድርሻዬን ይዤ

ተታሎ ልቤ በዓም ተይዤ ስቃይ

ሆነብኝ ስቃይ ሞት ከበበኝ

ቀኑም ሌሊቱም ጨለመብኝ

ልቤን መልሸየ እቤቱ ስገባ

ድግስ ደግሶ ተቀበለኝ አባ

ልቤን መልሸየ እቤቱ ስገባ

ድግስ ደግሶ ተቀበለኝ አባ

ባወዳድስ ባሞጋግስህ ዝምብዬ አይደል አለኝ ምክንያት

ሁሌ ይደንቀኛል ፍቅሩ ምሕረቱ ፍጥረት ይዘምር ይስገድ በፊቱ

ሳዝን ስጨነቅ ዉስጤ ሲከፋ

መስቀሉን ሳየዉ አገኘዉ ተስፋ

ያባብለኛል ልጄ እያለ

በቃሉ እያዘለለ

እንዳልረበሽ ዉስጤም እንዳይፈራ

ያሳድረኛል በክንፎቹ ጥላ

እንዳልረበሽ ዉስጤም እንዳይፈራ

ያሳድረኛል በክንፎቹ ጥላ

ባወዳድስ ባሞጋግስህ ዝምብዬ አይደል አለኝ ምክንያት

ሁሌ ይደንቀኛል ፍቅሩ ምሕረቱ ፍጥረት ይዘምር ይስገድ በፊቱ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ