አምጡ በገና
Amtu Begena
2016 · ትራክ 1 · 4:51 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምጡ በገና ምክንያት አለኝ ለመደርደር
መዳኔ ብቻ በቂ ነዉ ለእኔ ለመዘመር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አረሳዉም እኔ ያኔ ለእኔ የሞተዉ ስለ እኔ
እንደዉ ቀላል አይደል ይሄ ሚስጥር የዳንኩበት ቀኔ
ከዚህ ሌላ ደስታ የለም ለእኔ ልጁ የመሆኔ
ድስ ደስ ይለኛል ይሄን ሳስብ በቂ ነዉ መዳኔ
ተነሺ ይለኛል ለጌታ ዘምሪ ያደረገልሽን
ማዳኑን አዉሪ ከበሮ ይመታ በገናዉ
ይደርደር ምስጋዉን አምጡ ለስሙ ይዘመር
እንደ እኔ ያሉ ይዘምሩ
ከሞት የዳኑ ይዘምሩ
ለምስጋና ኑ ይዘምሩ
ለእርሱ ዘምሩ ይዘምሩ (፪x)
አዝማች · Chorus
አምጡ በገና ምክንያት አለኝ ለመደርደር
መዳኔ ብቻ በቂ ነዉ ለእኔ ለመዘመር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰላሜን ሊያጠፋ ሊሰርቀኝ ጠላቴ ቢዞርም
ዉስጤ ተደላድሏል ተደግፎ በእግዚአብሔር
የሚታየዉ ነገር የሚሰማዉ አይደል ማስረጃዬ
እንደ ወንዝ የሚፈስ ደስታ አለኝ ይምስገን ጌታዬ
ተነሺ ይለኛል ለጌታ ዘምሪ ያደረገልሽን
ማዳኑን አዉሪ ከበሮ ይመታ በገናዉ
ይደርደር ምስጋዉን አምጡ ለስሙ ይዘመር
እንደ እኔ ያሉ ይዘምሩ
ከሞት የዳኑ ይዘምሩ
ለምስጋና ኑ ይዘምሩ
ለእርሱ ዘምሩ ይዘምሩ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ