አዶናይ
Adonay
2010 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሰማይ ነበር የተላከ ከሰው ተወልዶ ለሰው ሞተ
ከሞት ተነሳ ከእዛ አረገ ከአባቲ ቀኝ ተቀመጠ
ለዘመናት ቀል የነበረ ከእቅፉ ወጥቶ መጥቶ ተረፈ
አባትን ከልጅ ያስታረቀ ከኢየሱስ ሌላ ጌታ የታለ
አዝማች · Chorus
አሃሃ አዶናይ (፬x)
የለም እንዳንት ምድር ላይ
የለም እንዳንተ በሰማይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለሁለት ጌቶች ለመገዛት ህጉ አይፈቅድም ይከለክላል
አንዱን ይይዛል ያን ይተዋል ለፈቀደለት ባርያ ይሆናል
ሚስጥሩ ገብቶኝ መረጥኩኝ ሌላውን ትቼ እርሱን ሾምኩኝ
ኢየሱስ ጌታ ሲሆንልኝ የቀረው በሥሙ ተገዛልኝ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴ በእኔ ላይ (፬x)
አድርጌሃለሁ የበላይ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስኪ የቱ ነው የትኛው
በፊቱ ከብዶ ሚታየው
ሁሉን ይችላል ብቃት አለው
ስለእግዚአብሔር ነው የምናገረው
እኔም አየሁት በሕይወቴ
ተዛዝ አውትቶ ሲሰራ አንዴ
ታሪክ ሲነበብ ቀን ሲታይ
እርሱ ብቻ ነው አልሻዳይ
አዝማች · Chorus
አይ ኤሄሄ አልሻዳይ (፬x)
የለም እንዳንት ምድር ላይ
የለም እንዳንተ በሰማይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ