እቀድስሃለው
Eqedesehalew
2010 · ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ
በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ድሮ ትዝ ይለኛል በፊት ገና ያኔ
መስዋእቴን ለካህንህ ስሰጥ እኔ ውጭ ቆሜ
ካህኑ የገባው እየቀደሰህ
እኔም እመኝ ነበር ክብርህን ማየት
ዛሬማ ሆነልኝ እኔም በልጅህ
ደፍሬ እንድገባ ወደ መገኛህ
አዝማች · Chorus
እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ
በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙዎች ያመልካሉ ስለማያውቁት
ስፍራን ይመርጣሉ ለማቅረብ ለአንተ ስግደት
እኔ ግን እያወኩ ገብቶኝ ማንነትህ
በመንፈስ በእውነት ወደድኩኝ ላመልክህ
ካህን አልፈልግም ረዳትስ ለእኔ
እቀድስሃለሁ ብቻዬን መጥቼ
አዝማች · Chorus
እቀድስሃለው እግዚአብሔር አምላኬ
በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መስዋእት አለ ከኔ ለአንተ ምሰጥህ
ስለ አደረክልኝ አይደል ገብቶኝ እንጂ ማንነትህ
በግሌ አወቅኩህ ወደድኩህ ከልቤ
በማወቅ ተናገርሁ አምላኬ ነህ ብዬ
በማወቅ ተናገርሁ አዳኜ ነህ ብዬ
በማወቅ ተናገርሁ ጌታዬ ነህ ብዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
እቀድስሃለው (፫x) ጌታዬ
ቁጥር 5 · Verse 5
በውጪ አይደለም ማደሪያህ ገብቼ ገብቼ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ