ሰማያዊ ዜግነት
Semayawi Ziegenet
2010 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አዲስ ልዩ ነገድ ተገኝቷል
ከአስራ ሁለቱ አይደል ከእስራኤል (፪x)
እጅግ ልዩ ነው ዐይነቱ የነገዱ
ሃያል ገናና ነው ንጉሡ
የጸና መንግሥቱ (፪x)
ዜግነት ቢሉ ሰማያዊ
አለቃው የሰማይ የምድር ፈጣሪ
አለ የሚኖር ዘለዓለማዊ
አዝማች · Chorus
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደዚህ መንግሥት ሲጋብዘኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ዜግነት እስኪሰጠኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደዚህ ግዛት ሲጋብዘኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ማንነት እንዲሰጠኝ
እኔም ግዛቱ ለመግባት አሰብኩኝ
ህገመንግሥቱን አነበብኩኝ የተጻፈውን አንበብኩኝ
መግቢያው መወለድ ነው ዳግም
የመስቀሉን ሃይል አምኖ መቀበል (፪x)
መቀበል ማመን በልጁ
በመንፈስ ዳግም መወለዱ
ሌላም አይደለም ይሄው ነው መንገዱ
አዝማች · Chorus
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) በማመን ብቻ ሲቀበለኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ልጁን ስቀበል ተ???በለኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) አባቴ ሆኖ ልጄ ሲለኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ለዘለዓለም ኑሪ ሲለኝ
ጽዮናዊ ነኝ በዜግነት አሁንማ
ተረሳስተናል ከዓለም ጋራ ተካክደናል ከዓለም ጋራ
ሰማያዊ ነው ሚናፍቀኝ የማስበው
የምድርን ንቄ ትቼዋለሁ ጽዮንን ተመኘሁ (፪x)
ጨለማው ጠፍቶ በርቻለሁ
ሰማያዊ ነው የምናገረው
ስፍራ ቀይሬ በቀኙ ሆኛለሁ
አዝማች · Chorus
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) በቀኙ በኩል አስቀመጠኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ቋንቋዬን ሁሉ ቀየረልኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) አዲስ ማንነት አገኘሁኝ
(አስገረመኝ አስደነቀኝ) ወደ መንግሥቱ ገላገለኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ