አለኝ ለአንተ ምሥጋና
Alegn Lante Mesgana
2010 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
አለኝ አለኝ አለኝ ለአንተ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ገና በልጅነት በልጅነት ስለለመድኩኝ
ውለታህን እያሰብ እያሰብ አመሰገንኩኝ
አሁን የምሥጋና ጥቅሙ ኃይሉ ሲገባኝ
ከነገሬ በፊት አስቀድሜ አመሰገንኩኝ
ምሥጋና ሲቀድም ሲወጣ ሲሆን መጀመሪያ
አውቃለሁ በረከት . (1) . ፈጥኖ ለእኔ እንደሚመጣ
አዝማች · Chorus
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
አለኝ አለኝ አለኝ ለአንተ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጠብቄ ጥያቄዬ ጥያቄዬ ሲመለስልኝ
ምሥጋና ለአምላኬ ለአምላክ ሠጥ ቆየሁኝ
ዛሬ ግን ሲገባኝ ሲገባኝ ሲገለጥ ነገሩ
በልጅ አንደበቴ አንደበት ምሥጋና ማኖሩ
ጠላት ምቀኛዬ ምቀኛዬ ለማጥፋት ነው ለካ
ስለዚህ ላመስግን ላመስግነው በምንም ሁኔታ
አዝማች · Chorus
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
አለኝ አለኝ አለኝ ለአንተ ምሥጋና (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፊቴ የቆመው ተራራ አይደለውም መናዱ
ከሰማይም መና ወይም ሥጋ አይደለም መውረዱ
ተራራው ሳይናድ ሳይናድ መናው ሳይወርድልኝ
ይሁዳን ከፊቴ ከፊቴ አስቀድማለሁኝ
ምሥጋና ሲቀድም ሲወጣ ሲሆን መጀመሪያ
አውቃለሁ በረከት . (2) . ፈጥኖ ለእኔ እንደሚመጣ
አዝማች · Chorus
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
ከውስጤ የሚፈልቅ ከልብ የሚወጣ
አለኝ አለኝ አለኝ ለአንተ ምሥጋና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ