ቅርቤ ነህ
Qerbie Neh
2010 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማያትን ቀና ብዬ እንደማይ
ሳየውም ሩቅ እንደሆነ
አምላኬ እንደእዛ አላይህም
እግዚአብሔር እንደእዛ አላርቅህም
ቅርብ ነህ ለእኔ አለህ አጠገቤ (፬x)
ሰማይ ሰፋህ አልለው ትልቅ ነህ ጌታዬ
ግን መረጥክ ልትገባ ልትቆይ ከልቤ
የታሰበ ኧረ ነው ለአንተ የተዘጋጀ
ስለዚህ አውቃለሁ አጠገቤ እንዳለህ
አዝማች · Chorus
ቅርቤ ነህ ከጐኔ ነህ (፪x)
ይሰማኛል ህልውናህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የጠየኳቸው ጥያቄዎች ሁሉ
መልስን ብትሰጣቸው ወይም ቢዘገዩ
እነሱንም አይቼ ቅርቤ አላልኩህም
እስከ ፍጻሜ ከእኔ ጋር ነህ አመንኩት ቃልህን
አዝማች · Chorus
ቅርቤ ነህ ከጐኔ ነህ (፪x)
ይሰማኛል ህልውናህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ