ቃልኪዳን ገባሁኝ
Qalkidan Gebahugn
2010 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔ የእርሱን ላውጋው የፈጠረኝን
እርሱም ስለእኔ ሁሉን ሊያውቅልኝ
ስምምነት አደረኩ ቃልኪዳን ገባሁኝ
እግዚአብሔርን ብቻ ላውቀው እርሱም ለእኔ ሊያውቅልኝ
አዝማች · Chorus
ቃልኪዳን ገባሁኝ (፪x)
እኔ የእርሱን ብቻ ላውቀው
እርሱም ለእኔ ሊያውቅልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰማሁት ጥበብ የተቀበልኩት
በፈጠረኝ ጌታ ሲታይ ሞኘነት
እስከዛሬ ለእኔ አውቄ የአደኩበት
ገባኝ መልካምነት ምንም እንደሌለበት
ስለዚህ ነው እኔን በቃ??? ወሰንኩት
አዳኜ አድርጌ የተቀበልኩት
አዝማች · Chorus
ቃልኪዳን ገባሁኝ (፪x)
እኔ የእርሱን ብቻ ላውቀው
እርሱም ለእኔ ሊያውቅልኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ልክ እንደእረኛ የሚሄድ ፊት ፊቴ
ከጐኔ እንዳላጣው አብሮኝ ሁልጊዜ
ሳጠፋ ስሳሳት ሳለሁ በድካሜ
ዞር ስል ምህረቱ የለ ከኋላዬ
እንደእርሱ ያለ አምላክ ከየት አገኛለሁ
ምህረቱ አስደናቂ ለዘለዓለም ነው
አዝማች · Chorus
ቃልኪዳን ገባሁኝ (፪x)
እኔ የእርሱን ብቻ ላውቀው
እርሱም ለእኔ ሊያውቅልኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለእናንተስ ዕውቀት ማነው የነገራቹህ
ስለእናንተ ሕይወት ጠልቆ ሚያውቅላቹህ
ጠጋ በሉት እርሱን ሩህሩህ ባሕሪውን
የሰዎች ጥያቄ ችግር ሚገባው
ከእስትንፋስ የሚቀርብ ፍቅርን የተሞላ
ማይሰለች ወዳጅ ነው እመኑበት ብቻ
ቁጥር 5 · Verse 5
ቃልኪዳን አድርጉ ከእርሱ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እስከ መቼም አይጥላቹህ
እርሱ ይሁን እረኛቹህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ