የጠፋው ልጅ
Yetefaw Lej
2010 · ትራክ 6 · አማርኛ
ምን አጣሁኝ ብለህ ወጣህ ከአባትህ ቤት
ሄድክ ርቀህ ሰላም ደስታ ወደ ሌለበት
አባትህ አሁንም እቤት ካሉት ይልቅ
ያሰባል ሰለአንተ ይናፍቃል ይጠብቃል
ሚመለሰው ልጄ መቼ ነው እያለ
የጠፋው የእግዚአብሔር ልጅ አንተ አይደለህ ወይ
መመለስህን ሁልጊዜ ይናፍቃል ሊያይ
መመለስህን ሁልጊዜ እግዚአብሔር ይናፍቃል ሊያይ
ና ተመለስ ሁሉን ትተህ እርሳውና
የአባትህ እጅ ዛሬም ለአንተ ነው እንደተዘረጋ
በትር ይዞ እኮ አይደለም ሚጠብቅህ
ታውቀዋለህ አንዳይለወጥ እግዚአብሔር እንደሚወድህ
"ወንድሜ ብዙዎች በቤቱ ቢኖሩም
ስለጠፋኀው ስለአንተ ዘወትር ያስባል
ወደ ቤቱ የምትመለስበትን ሰዓት ይጠባበቃል
የክብር ልብስ ሊያለብስህ
የምህረት ደጆቹ ሁልጊዜ ለአንተ ክፍት ናቸው
በአባትህ ቤት መኖር ለአንተ ይሻልሃል
ወስነህ እንዲ በል"
አዝማች · Chorus
ኢሄው መጣሁ ወደ ቤት
ተመልሻለሁ እንድትምረኝ
በክርስቶስ አስቀድሜ ተይቃለሁ
እኔም ልጅህ ናፍቄያለሁ
አባቴ አንተን ይሄው ልጅህ
መጥቻለው ብትቀበለኝ
ወድሃለሁ (፪x) እግዚአብሔር ወስኛለሁ
አዲስ ጉዦ ከአንተ ጋራ ልጀምር ወስኛለሁ
አዲስ ጉዦ ከአንተ ጋራ ልጀምር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ