ትልቅ አንተ ብቻ
Teleq Ante Becha
2010 · ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (፬x)
አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጉልበተኛ ነው ከተባለ ምንም ነገር
ተለካክቶ ነው ተወዳድሮ ከሌላው ጋር
አንተ ምድርን ሰማያትን እንኳን ስጸራ
የተጠቀምከው ቃልህን ነው ከአፍህ የወጣ
ቃልህ ያልተፈጠረውን መፍጠር ከቻለ
እንዴት ትልቅ ነው ነገርህ ልበል ልናገር ለአንተ
አዝማች · Chorus
ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (፬x)
አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የአንተ የሆኑት ልጆችህ ከአንተ የወጡት
ቃልህን በውስጥ መንፈሳቸው ስላስቀመጡት
እነርሱ ሳይቀር የአንተን ቃል ሲናገሩት
ስጋን ተላብሰው ሰራዊት ሆኗል ደረቅ አጥንት
ዝናብ እንዳይወርድ ተከልክሎ ፀሐይ ቆማለች
አይደለም አንተ ልጆችህ ናቸው ሃይለኞች
አዝማች · Chorus
ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (፬x)
አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀላል ነው በአንተ እይታ ሳየው
ይሆናል ቃል ስትወጣ ወዲያው
ባለ ስልጣን ነህ እግዚአብሔር ባለስልጣን
ግር ግር የለም ስትናገር ሁሉ ይሰማል
ይሆንልሃል እንደአፍህ አንተ እንዳልከው
ስላመንኩብህ አንተን ነው የማመልከው
አዝማች · Chorus
ትልቅ አንተ ብቻ ነህ ትልቅ ትልቅ (፬x)
አይችልም ምንም ማንም ከአንተ ሊልቅ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ