አመሰግናለው
Amesegenalew
2010 · ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ሕይወትን ሰጥተኀኝ በመስቀል ላይ ሞትክና
ዋጋዬን ከፈልክልኝ አስታረቅከኝ ከአብ ጋር
በኀጢአት የጠፋውን ያጣሁትን ማንነቴን
አገኘሁት በአንተ ሆነኅልኝ መስዋእቴ
ሚስጥርህን ገለጥክልኝ መጥተህ መንፈስ ቅዱስ
ኢየሱሴን አምኜው ወስኜ ስቀበል
ከዛ ቃልህን ከፍቼ መረዳት ስጀምር
ለእኔ ያሰብከው ሁሉ ይገለጥልኝ ጀመር
አዝማች · Chorus
አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እንዴት ብዬ ዝም ልበል አስቸገረኝ መደበቁ
የበራልኝ እውነት እኮ ያስገርማል ከሌሎቹ
እንዴትስ ይደበቃል ኧረ መቼ ተችሎ
ለብዙዎች ሚስጥር ሲሆን ሳየው ለእኔ ግን ተገልጦ
አዝማች · Chorus
አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
የበላይ እግዚአብሔር የለም አንተን ሚመስልህ
ገና እስከዘለዓለም አንተ ትመለካለህ
አመታት ተሰጥተውኝ ብናገር ብጨምር
እንዴት ብዬ አውርቼ ስለአንተ ልፈጽም
አዝማች · Chorus
አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
የሆንክልኝ ለእኔ ከአይምሮዬ በላይ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ