አዋቂ ነው
Awaqi Neh
2010 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (፭x)
አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ጽንሷ መዘግየቱ ያሳዝናል
ሃና ባትረዳ ባይገባት
ጌታ በእርሷ ያየው ትልቅ ሰው
አስቦ ነው እንጂ ለእራሱ ሊለየው
ረስታ ሃና የእግዚአብሔርን አዋቂነት
ካሰበችው በላይ ሲሆን ድንገት
የእርሱ ስራው ለጊዜ አስደናቂ
አለች እርሷም ግርም ሲላት ኧረ አዋቂ
አዝማች · Chorus
አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (፭x)
አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ኤልያብ ነው በሰው ሚዛን የበለጠው
በነቢዩ ዐይን እንኳን ቀድሞ የገባው
ፊትን አልፎ ሚመረምር የልብን
እግዚአብሔር ግን መረጠው ዳዊትን
የጓዳውን ሰው ሳያየው ስለሚያውቀው
እረኛውን በስልጣን ላይ አስቀመጠው
ጠብቆ ሁሉን ነገር ስለሚያውቀው
ሲመርጥ እርሱ አይሳሳትም አዋቂ ነው
አዝማች · Chorus
አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (፭x)
አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
የትኛውን ነገሬን ነው ምደብቀው
እግዚአብሔር ሁሉን ያያል አዋቂ ነው
በሰዎች መመረጥ ቀርቶብኝ
ይሁንልኝ እግዚአብሔር ያየልኝ
ጅማሬውን ፍጽሜውን ስለሚያውቀው
ይሻለእኛል ምንም ቢሆን እርሱ ያለው
መልካም ስለሆነ የሚያስበው
የመረጠው እርሱ ለእኔ ምርጫዬ ነው
አዝማች · Chorus
አዋቂ ነው የኔ ጌታ አዋቂ ነው (፭x)
አዋቂ ነው እግዚአብሔር አዋቂ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ