Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልቸኩልም

Alchekulim

2007 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2

ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2

ቸኩዬ ወጥቼ ምን አግኝቼ አውቃለው

ጌታዬን ጠብቄ ሁሉን አግኝቻለው

ባለፈው ዘመኔ አወኩ አንድ ነገር

ጌታን ከጠበኩት እንደማያሳፍር

አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2

ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2

አሁኑኑ አግኝቼ ይዤ ካላየሁት

ያልኩትን ያን ነገር ጥሬ አገኘሁት

ታምር መስሎ የታየኝ እንዲያ ያጣደፈኝ

እጄ ላይ ሲገባ ቀሎብኝ ሰለቸኝ

አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2

ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2

እኔ ተጣድፌ ያመጣሁት ነገር

አይሁት ከእጄ ላይ ወድቆብኝ ሲሰበር

የጠበኩት ያንን የእግዚአብሔርን ነገር

ሲመጣም ደስ ይላል ፀንቶ ስለሚኖር

አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2

ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ