Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሌላው አልመች አለኝ

Lelaw Alimech Alegn

2007 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ልቤ ገብቶ ስላስደነቀኝ

ሌላው ሌላውማ አልመች አለኝ

ጌታ ልቤ ገብቶ ስላስደነቀኝ

ሌላው ሌላውማ አልመች አለኝ/4

ቢያድነኝም ባያድነኝም

ሰው ለቀረፀው ፈፅሞ አልሰግድም

ቢያድነኝም ባያድነኝም

ለውርቁ ምስል ፈፅሞ አልሰግድም

አንዴ አጎንብሼ ሳመሰግነው

ደግሞ ቀና ስል እርሱ ሌላ ነው

እንዴት ልነሳ እዛው ቀረሁኝ

መኖር ለምጄ እያመለኩኝ

ጌታ ልቤ ገብቶ …

ቢያድነኝም ባያድነኝም …

ቀንና ለሊት ቢሰገድለት

የማይሰለች ክብር አለበት

መኖሬን ሳስብ እርሱ ባለበት

ሃሴት አደረኩ ነፍሴም ደስ አላት

ጌታ ልቤ ገብቶ …

ቢያድነኝም ባያድነኝም …

ፀሃይዋንና ጨረቃዋን

የሚያስፈጉን ልብርሃን

በጉ ባለበት አያስፈጉም

ስለሚያበራ ለዘላዓለም

ጌታ ልቤ ገብቶ …

ቢያድነኝም ባያድነኝም …

ጊዜያዊ ደስታ ለሚሰጠው

ልቤን አልጥልም ለሚጠፋው

በዙፋኑ ፀንቶ ለሚኖት

ጨክኛለሁኝ እርሱን ለማክበር

ጌታ ልቤ ገብቶ …

ቢያድነኝም ባያድነኝም …

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ