አምልኮ ለጌታ ነው
Amleko Legieta New
2007 · ትራክ 6 · 7:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እወድሀለው ብዬ ለአንተ ብዘምር
ማነው ሚከራከር ማነው ሚለው ቅር (፫x)
ይወራ የጌታዬ ሥራ
ይወራ የአምላኬ ሥራ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው ዝም ብሎ ይከራከራል
ጌታውን ለማምለክ ጥቅስ ያወጣጣል
አንዱ እንዲህ ነው ሲል ሌላው እንዲያ ይላል
አምልኮ ለጌታ ነው ሰውን ምን ነክቶታል
በመንፈስ ይሁን እንጂ እየሱስ ተመችቶታል
(የእኔ ጌታ) አምላኬ ተቀብሎታል
እየሱስ ተመችቶታል (ኢየሱስ) አምላኬ ተቀብሎታል
አዝማች · Chorus
እወድሀለው ብዬ ለአንተ ብዘምር
ማነው ሚከራከር ማነው ሚለው ቅር (፫x)
ይወራ የጌታዬ ሥራ
ይወራ የአምላኬ ሥራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጡት ከሚጠቡት ከህፃናቱ
ምስጋናን ለእርሱ ማዘጋጀቱ
ገብቶት እኮ ነው አይደለም በከንቱ
አምልኮ ምስጋናቸው ገብቷል ፀባኦቱ
ለእኛ አይግባን እንጂ ወዶታል ይሄ ክንዴ ብርቱ
ወዶታል እየሱስ ብርቱ (፫x)
አዝማች · Chorus
እወድሀለው ብዬ ለአንተ ብዘምር
ማነው ሚከራከር ማነው ሚለው ቅር (፫x)
ይወራ የጌታዬ ሥራ
ይወራ የአምላኬ ሥራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ብልቃጡን ሰብራ ሽቶ አፈሰሰች
ድሮ በሚያውቋት እየተተቸች
የጌታዋን እግር መሳሟን ቀጠለች
እየሱስ ተደነቀ በሰላም ሂጂ አላት
በተቺዎቿ ፊትም ጌታዬ መሰከረላት
(የእኔ ጌታ) አባቴ ልክ ነሽ አላት
ኢየሱስ (ኢየሱስ) መሰከረላት አባቴ መሰከረላት
አዝማች · Chorus
እወድሀለው ብዬ ለአንተ ብዘምር
ማነው ሚከራከር ማነው ሚለው ቅር (፫x)
ይወራ የጌታዬ ሥራ
ይወራ የአምላኬ ሥራ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔን ያዳነኝ የደሙ ሚስጥር
ገብቶኝ እኮ ነው የውዴ ፍቅር
ምስጋና አምልኮዬ ለጌታዬ ክብር
ንገሥ በሕይወቴ ላይ ክበር ጌታ እየሱስ
አምልኮ ለአንተ ብቻ ለሌላ እኔ አለስቀምስ
(ለመላዕክት) ለሌላ እኔ አለስቀምስ
(ለሰማዕቶት) ለሌላ እኔ አለስቀምስ
(ለመላዕክት) ለሌላ እኔ አለስቀምስ
(ለሰማዕቶት
አዝማች · Chorus
እወድሀለው ብዬ ለአንተ ብዘምር
ማነው ሚከራከር ማነው ሚለው ቅር (፫x)
ይወራ የጌታዬ ሥራ
ይወራ የአምላኬ ሥራ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ