እግዚአብሔር ዘመዴ
Egziabher Zemede
2007 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘማሪው ሲዘምር እጁን ሲዘረጋ
ያደረገለትን በቅኔ ሲያወጋ
እኔም ተስማምቼ መዘመር ጀመርኩኝ
እግዚአብሔር ዘመዴ ዘመዴ ነው አልኩኝ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ዘመዴ አይደለም ወይ/4
ባለቅኔዎች ዘመሩለት
እግዚአብሔር ዘመዳችን ነው አሉ/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ታዲያ እኔስ ምነው ብዘምር
ቅኔና በገናን ብደረድር
ሰባኪው ሲሰብክ ጌታን ሲተርከው
ለኔ እንደሞተ ፍቅር ግድ እንዳለው
እኔም ተደንቄ መስበኬን ጀመርኩኝ
አዝማች · Chorus
እየሱስ ያድናል ያድናል እያልኩኝ
እየሱስ ያድናል እያልኩኝ/4
ባለቅኔዎች ዘመሩለት
እግዚአብሔር ዘመዳችን ነው አሉ/2
ቁጥር 3 · Verse 3
ታዲያ እኔስ ምነው ብዘምር
ቅኔና በገናን ብደረድር
ውለታው እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል
ፍቅሩ እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል
ማዳኑ እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል
ኧረ እንዴት/3 ይረሳል
ይደርደር በገና ይደርደር በገና
እኔም እንደዳዊት መዝሙር አለኝና
ይደርደር በገና ይደርደር በገና
ከሞት ያስመለጠኝ እየሱስ ነውና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ