Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከልጅነቴ ጀምሮ

Kelijinete Jemiro

2007 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከልጅነቴ ጀምሮ መንገድ የመራኝ

እንዳልሞት የጠበቀኝ አባት አለኝ

ያሳደገኝ/4

የለም የለም አዎ

የለም የለም

በሰማይ የለም እንዳንተ

በምድር የለም እንዳንተ

ተጨንቄ በምድረበዳ

አለቀስኩኝ ስለማልወጣ

ከሰማይ አየኝ አታልቅስ አለኝ

ለካ እኔስ አለኝ የሚያየኝ/2

ማነው ያከበረኝ እየሱስ ነው

ማነው ሰው ያረገኝ እየሱስ ነው/2

ከልጅነቴ ጀምሮ …

ያሳደገኝ/4

የለም የለም …

በሰው ሃገር ለሚንከራተት

ወዳጅ ዘመድ በሌበት

በሁሉም ስፍራ ላይ ሁልግዜ ሚገኝ

እራበኝ አበላኝ ጠማኝ አጠጣኝ እዚ አደረሰኝ

ለተራበው አጉራሽ እየሱስ ነው

ለተጠቃው ደራሽ እየሱስ ነው/2

ከልጅነቴ ጀምሮ …

ያሳደገኝ/4

የለም የለም …

የተረሳው የበግ እረኛ

ቸሩ እግዚአብሔር አሰባኛ

ካንበሳና ከድብ ያስጣለኝ ጌታዬ

ክበር እለዋለው እኔም በተራዬ ባለውለታዬ

የተረሳ አስታዋሽ እየሱስ ነው

እረኛን አንጋሽ እየሱስ ነው/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ