እንመለስ
Enimeles
2007 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምን አይነት ልብ ይዘን ምን እየሰራን ነው
በአምልኮ ስፍራ ሁሌ ምንገኘው
ጠብና ክርክር አለ በኛ መሃል
መዘመር ስንጀምር ጌታስ ምን ይለናል
ልብን ኩላሊትን የሚመረምረው
እርሱ አይታለልም ማንን ነው ምንዋሸው
አዝማች · Chorus
እንመለስ ሁላችንም
ቂመኝነት ለኛ አይሆንም
ጌታ ቆሞ ይለምናል
ስንመለስ ማየት ይሻል
ቁጥር 2 · Verse 2
አንዱ አንዱን ሲከሰው
ሲጥለው ሲተቸው
ሲያማው ሲያዋርደው
ነው እኮ ነው ሚታየው ሚሰማው
እስቲ እኛ እንዋደድ መርገሙን ይስበረው
በኛ ጠብ አያምርም ፍቅር ነው የሚያምረው
አዝማች · Chorus
እንመለስ ሁላችንም
ቂመኝነት ለኛ አይሆንም
ጌታ ቆሞ ይለምናል
ስንመለስ ማየት ይሻል
ቁጥር 3 · Verse 3
አንቀባበልም አገልጋይ ካገልጋይ
በጣም ያሳፍራል ስንቆም መድረክ ላይ
ይቅር ሳንባባል ታስረን ተቀምጠን
ስለፍቅር ሰብከን ፈውስ እንጠብቃለን
ፀሎት ብናስረዝም ባርከንም ብንለው
አንተ ማን ነህ ያላል ሁሉን አዋቂ ነው
አዝማች · Chorus
እንመለስ ሁላችንም
ቂመኝነት ለኛ አይሆንም
ጌታ ቆሞ ይለምናል
ስንመለስ ማየት ይሻል
ቁጥር 4 · Verse 4
ወንጌሉን አስቀምጠን ትልቁን ስራችን
እየተካሰስን እርስ በእርሳችን ጉዳችን
እስቲ እኛ እንታረቅ
እንልመድ ማለትን
ያለፈው ይረሳ
ሁሉም እጁን ያንሳ
አዝማች · Chorus
እንመለስ ሁላችንም
ቂመኝነት ለኛ አይሆንም
ጌታ ቆሞ ይለምናል
ስንመለስ ማየት ይሻል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ