እንዴት ሰው ሳያነብ
Endiet Sew Sayaneb
2007 · ትራክ 2 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ላምልከው (፭x)
በመንፈስ ሁኑና ጌታን አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ሁኑና ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ያስመለጠኝ እየሱሴ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ በሉት
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታን ማገልገሉ ምን ጠቀመው ሲሉኝ
ጌታን መከተሉ ምን ረባው ሲሉኝ
የተፃፈልኝን ቃል አነበብኩኝ
እንዳገለግለው የባሰ አበረታታኝ
በምድር መቶ እጥፍ (አሜን)
በሰማይ ቤት አለኝ
በምድር መቶ እጥፍ (አሜን)
በሰማይ ቤት አለኝ
በሰማይ ቤት አለኝ
አዝማች · Chorus
በመንፈስ ሁኑና ጌታን አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ሁኑና ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ያስመለጠኝ እየሱሴ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ በሉት
ቁጥር 3 · Verse 3
እምነት ከመስማት ነው
መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው
እንዴት ሰው ሳያነብ ከአያቱ ይወርሳል
እውር እውርን ሰው ወዴት ይመራዋል
ተያይዞ ገደል በለው ኃላን ይቆጭሃል
እውነቱን ልንገርህ (እውነቱን) እየሱስ ያድናል (አሳምሮ)
እውነቱን ልንገርህ (እውነቱን) እየሱስ ያድናል (አሳምሮ)
ኢየሱስ ያድናል
አዝማች · Chorus
በመንፈስ ሁኑና ጌታን አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ሁኑና ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ያስመለጠኝ እየሱሴ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ በሉት
ቁጥር 4 · Verse 4
ልቤን ስለጣልኩኝ ብሉይ ኪዳን ላይ
በጥላው ረክቼን አዲስን ሳላይ
በእራሴ እንዳልወስን ነበሩኝ ከልካይ
ይሉኝታው ለቀቀኝ (እሰይ) እየሱስን ሳይ
ይኸው ስንት አመቴን (ሳይሰለቸኝ) ሆንኩኝ የእርሱ አገልጋይ (ተመችቶኝ)
ይኸው ስንት አመቴን (ሳይሰለቸኝ) ሆንኩኝ የእርሱ አገልጋይ (ተመችቶኝ)
ሆንኩኝ የሱ አገልጋይ
አዝማች · Chorus
በመንፈስ ሁኑና ጌታን አመስግኑት (አመስግኑት)
በመንፈስ ሁኑና ለእርሱ ተቀኙለት
ከሞት ያስመለጠኝ እየሱሴ በሉት (፪x)
ኢየሱሴ በሉት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ