ሃይለኛ
Haylegna
2007 · 4:45 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሃይለኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
ቁጥር 1 · Verse 1
አንደኛ የምለው በኔ ህይወት ላይ
የይሁድ አንብሰሳ እርሱ አይደለም ወይ
ሞት በኔ ሲኩራራ እኔን ሲያስፈራራ
መቃብር ፈንቅሎ ሞትን በሞት ገሎ
እየሱስ አንደኛ እኔን አስከትሎ
አዝማች · Chorus
አንደኛ/12
ሃይለኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ እሞታለው ደሞም እነሳለው
ያለው ትዝ ብሏቸው መቼ ተረጋግተው
ተመካክረው ገለው አፈር ገባ ብለው
ተደርጎ የማያውቅ መቃብር ሲጠበቅ
እየሱስ ተነስቷል አለም ሁሉ ይደነቅ
አዝማች · Chorus
ተነስቷል/12
ሃይለኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታዬ አሸንፎ እኔ ተሸለምኩኝ
ካሸናፊዎቹ ሁሉ አስበልጦኝ
ሰባሪው ከፊቴ አለፈ አባቴ
እኔም ተከተልኩኝ አብሬው ገባሁኝ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
አዝማች · Chorus
አመለጥኩ/12
ሃይለኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
በሁሉ ነገር እየሱስ አንደኛ/4
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ