Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኧረ እኔስ ልባርከው

Ere Enes Libarkew

2007 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምንጭ ከዚያም ከዚም የሚፈልቅለት ሰው

አደረገኝ እግዚአብሔር

ኧረ እኔስ ልባርከው

እስቲ እኔስ ልባርከው/2

ጌታ ምንጭ አፍልቆ እኔን ሲባርከኝ

ጠላቶቼ መተው ሲናጠቁኝ

ደግሞ ሌላ ቦታ እርሱ ሲያፈልቅልኝ

ጠላቶቼ መተው ሲናጠቁኝ

መጨረሻን ሚያሳምረው

ድንቅ አድራጊው ጌታ እኮ ነው

ረሆቦት አደረገው/5

ምንጭ ከዚያም ከዚም የሚፈልቅለት ሰው

አደረገኝ እግዚአብሔር

ኧረ እኔስ ልባርከው

እስቲ እኔስ ልባርከው/2

ልጆቿን ሊውስድ ባለዳ መጣባት

የምትከፍለው ገንዘብ ስለሌላት

ቁጠባ የማያውቅ የነብይ ሚስት ናት

ባሏ ሲሞት የለም ያወረሳት

የእግዚአብሔር ሰው ፀለየላት

ዘይት ከላይ ፈሰሰላያ

እዳ ከፍላ እስኪተርፋት/5

ምንጭ ከዚያም ከዚም የሚፈልቅለት ሰው

አደረገኝ እግዚአብሔር

ኧረ እኔስ ልባርከው

እስቲ እኔስ ልባርከው/2

የሚዘጋው የለም የሚከፍተውን

ከፈተልኝ ጌታዬ በሩን

ጠላቴን መታና የዘጋብኝን

ከፈተልኝ የበረከቱን

ለታመኑት ሚታመነው

የተዘጋን የሚከፍተው

የሚያኖረኝ እየሱስ ነው/5

ምንጭ ከዚያም ከዚም የሚፈልቅለት ሰው

አደረገኝ እግዚአብሔር

ኧረ እኔስ ልባርከው

እስቲ እኔስ ልባርከው/2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ