Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንተማ አትታማ

Antema Atitama

2007 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቀኑ ሲከፋ ጊዜው ሲረዝም

ጌታ ትቶኛል ብዬ ስቆዝም

በጊዜው ደርሰህ ውብ አድርገሃል

ድንቅ አድራጊ ነህ አንተን ማን ያምሃል

አንተማ (፫x) አትታማ (፪x)

ጌታማ አይታማ (፬x)

ተስፋው ሲዘገይ ሲጨልምብኝ

ብዬው ነበረ ጌታን ግደለኝ

ሌቱ ሲነጋ ሁሉም ሲቀየር

ብዬ ፀለይኩ እድሜዬን ጨምር

አንተማ (፫x) አትታማ (፪x)

ጌታማ አይታማ (፬x)

የታመንንበት ተስፋ ያረግነው

ሞተብን ብለው አዝነው ጠውልገው

ድንገት ተገልጦ መካከላቸው

በሶስተኛው ቀን አሳፈራቸው

አንተማ (፫x) አትታማ (፪x)

ጌታማ አይታማ (፬x)

ለሚበላና ለሚጠታዉ

እንዴት ይታማል ጌታ እኮ ነው

ንፋስ ሳይታይ ዝናብም ሳይኖር

ምንጭን ያፈልቃል ከደረቅ ምድር

አንተማ (፫x) አትታማ (፪x)

ጌታማ አይታማ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ