Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልችልም

Alchelem

2009 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አስቤ አስቤ ብናገር ያወቅኩትን ሁሉ

አንድ እያልኩ እየቆጠርኩ ለማስረዳት ብሞክር

አልችልም ስለአንተ ለመግለጽ

አልችልም ዕውቀቴም ውስን ነው

ንፋስ ከየት እንደሚነፍስ ወዴት እንደሚሄድ

ለማወቅ እንደሚከብ በእጅም ለመጨበጥ

አልችልም ስለአንተ ለመግለጽ

አልችልም ዕውቀቴም ውስን ነው

አንተ በሰማይ ነህ ምድርንም ሞልተህ

ስለአንተ ለመናገር ብቁም አይደለሁም

አልችልም ስለአንተ ለመግለጽ

አልችልም (አልችልም) ዕውቀቴም ውስን ነው

አልችልም (፬x)

አልችልም (አልችልም) ዕውቀቴም ውስን ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ