Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፀሎቴ

Tselotie

2009 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተደላድሎ በምቾት በሃጢአን ድንኳን ከመኖር

መንፈስህ ባለበት በደጃፍህ ማደር

አንተ ባለህበት ከሆንን

በሰላም ወስጥ ማለፍን

ደስ የሚያሰኝህን ማየትም

እንደሚገባን መኖርን

እፈልጋለሁ (እፈልጋለሁ) ፀሎቴም ይሄው

ልመናዬ ልመናዬ ይህ ነው (፪x)

ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ በመንፈስህ ሙላኝ

በመንገድህም ምራኝ በሃይልህም አበርታኝ

ሁልጊዜ እንዳስብህ በፍፁም ልቤ እንድወድህ

እንደፈቃድህ እንድኖር ፍጻሜዬም እንዲያምር

እፈልጋለሁ (እፈልጋለሁ) ፀሎቴም ይሄው

ልመናዬ ልመናዬ ይህ ነው (፪x)

እፈልጋለሁ (፫x) ፀሎቴም ይህ ነው

እፈልጋለሁ (፫x) ፀሎቴም ይህ ነው

ግዕዝ???

. (1) .

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ