Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የመቶ አለቃው መዝሙር

Yemeto Aleqaw Mezmur

2009 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የኀጢአትን ጉልበት በሞቱ ሲሰብር

ይህን ጊዜ ተረዳሁ ጻድቅ እንደነበር

በመስቀል ላይ ሆኖ ነፍሱን ሲሰጥ ለእኔ

የፍቅሩን ልክ አየሁ አመንኩበት ያኔ

እንዲህ የወደደኝ ሳልወደው

ሕይወቱን የሰጠኝ ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)

የእኔን ሃፍረት ሊከድን ራቁቱን ሲሰቀል

አየእኔ አይታዋለች ቅጣቴን ሲቀበል

ጻድቅ ሆኖ ሳለ ሕይወቱን የሰጠው

የፍቅር ጌታ እንዴት ቢወደኝ ነው

እንዲህ የወደደኝ ሳልወደው

ሕይወቱን የሰጠኝ ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)

እኔን ለመታደግ ስቃዬን ሲቀበል

ፍቅሩ ግድ ይለኛል እንዴት ዝም ልበል

የሾህ አክሊል ደፍቶ ሲቆስል ሲደፋ

አምኜ ተናገርኩ ፍጥረት ይህን ይስማ

እንዲህ የወደደኝ ሳልወደው

ሕይወቱን የሰጠኝ ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)

እንዲህ የወደደኝ ሳልወደው

ሕይወቱን የሰጠኝ ኢየሱስ ብቻ ነው (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ