Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወድሃለሁ

Wedehalehu

2009 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በጨነቀኝ ጊዜ ወደአንተ ጮህኩኝ

ድምጼንም አድምጠህ ፊትም መለስክልኝ

እግሮቼንም አጸናህ እንዳልወድቅ ደገፍከኝ

ተመስገን (፪x)

ከብዙ ጥልቅ ውሃም በእጅህ አወጣኀኝ

ከብርቱ ጠላቶቼ ነጥቀህ አስመለጥከኝ

በመከራዬ ቀን ሃይሌ ሆንክልኝ

ተመስገን (፪x)

ወድሃለሁ በሙሉ ልቤ (፪x)

እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድሃኒቴ

አቤቱ ጉልበቴ ወድሃለሁ

ሁሁሁሁ (፪x)

አንተ ጨለማዬን ብርሃን ታደርጋለህ

የተዘጋውን ቅጥር ታዘልለእኛለህ

መጠጊያ ለሚያደርጉህ ጋሻ ትሆናለህ

ተመስገን (፪x)

ወድሃለሁ በሙሉ ልቤ (፪x)

እግዚአብሔር አለቴ አምባ መድሃኒቴ

አቤቱ ጉልበቴ ወድሃለሁ

ሁሁሁሁ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ