Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ቤትን

Egziabhier Bieten

2009 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ

እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂዎች በከንቱ ይደክማሉ

ሃብትና በረከት ከአባት ይወረሳል

መልካምን ሴትን ግን ማንስ ያገኛታል

ሃሃሃሃሃ ሃሃሃሃሃ

እግዚአብሔር በረከትን ካልሰጠ

ሰዎች ሁሉ በከንቱ ይሮጣሉ

የግዚአብሄር በረከቱ ታላቅ ናት

በእርሷም ዘንድ ሃዘንም የለባት

ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ የላቀ ነው

ለባሏም ዘውድ ናት ማንስ ያገኛታል

ሃሃሃሃሃ ሃሃሃሃሃ

እርሱ ግን በመንገዱ የሚሄድ

ፈቃዱንም የሚያደርግ

አምላኩን በፍፁም ልቡ የሚወድ

ለእርሱ ብቻ የሚሰጥ

እርሱ ያገኛታል ትዳሩም ይባረካል

በቤትም በከተማው ይሰምርለታል

ሃሃሃሃሃ ሃሃሃሃሃ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ