አልሻም
Alesham
2004 · ትራክ 1 · 6:39 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አልሻም ሌላ ሌላ ነገር
ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር
የበላይ ሆነህ በሕይወቴ
ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሌላውማ ሌላውማ
ከአንተ ውጪ ሌላ ሌላውማ
ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
ዓይኔን አንስቼ ከሌላው ላይ
ሾምኩህ ጌታዬ በልቤ ላይ
ግራ ቀኝ ብልም አያምርብኝም
ያለአንተ ለእኔስ አይሆንልኝም
እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ
ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ
አዝማች · Chorus
አልሻም ሌላ ሌላ ነገር
ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር
የበላይ ሆነህ በሕይወቴ
ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሌላውማ ሌላውማ
ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላውማ
ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
ልቤ ፅኑ ነው ተማመንኩብህ
ዘመኔን ለአንተ ይሄው ሰጠሁህ
ምራኝ ጌታዬ ወደ ወደድከው
እኔነት የለኝ ሁሉ የአንተ ነው
እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ
ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ
አዝማች · Chorus
አልሻም ሌላ ሌላ ነገር
ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር
የበላይ ሆነህ በሕይወቴ
ያንግስህ መላው እኔነቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ያሰብኩት ባይሆን የተመኘሁት
ሰላሜ በዛ በአንተ ያገኘሁት
አላማርርም ይሁን ያሰብከው
አላማህ ለእኔ ሁሌም በጐ ነው
እርካታዬ ነህ (፫x) እርካታዬ ነህ
ወግ ማዕረጌ ነህ (፫x) ወግ ማዕረጌ ነህ
አዝማች · Chorus
አልሻም ሌላ ሌላ ነገር
ምኞቴ አንተን ብቻ ማክበር
የበላይ ሆነህ በሕይወቴ
ያንግስህ መላው እኔነቴ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሌላውማ ሌላውማ
ከአንተ ውጪ ሌላ ሌላውማ
ገብቶኛል ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
አየሁት ለእኔ እንደማይስማማ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ