እወድሃለሁ
Ewedehalehu
2004 · ትራክ 9 · 5:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
(ኦሆ) አንተን አልኩኝ እኔስ (ኦሆ) በጠዋት በማታ
(ኦሆ) እረፍት ያገኘሁት (ኦሆ) በአንተ እኮ ነው ጌታ
(ኦሆ) አላማህ ገብቶኛል (ኦሆ) የሆንክልኝ ለእኔ
(ኦሆ) ዘምሬ አልጨርሰው (ኦሆ) በሕይወት ዘመኔ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
(አንተ) የሕይወቴ እረኛ አሃሃ
(አንተ) የነፍሴ ጠባቂ ኤሄ
(አንተ) ለክፉ ቀን ደራሽ አሃሃ
(አንተ) ምስኪኑን ታዳጊ ኤሄሄ
(አንተ) የደሃ አደግ አባት አሃሃ
(አንተ) ለተጠቃው ፈራጅ አሄሄ
(አንተ) እንባ የምታብስ አሃሃ
(አንተ) እውነተኛ ወዳጅ አሄሄ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
(ኦሆ) እወድሃለሁኝ (ኦሆ) ብርጫዬ ነህ ለእኔ
(ኦሆ) እንዳንተ አላየሁም (ኦሆ) ኢየሱስ መድህኔ
(ኦሆ) ሞቴን ሞተህልኝ (ኦሆ) በሕይወት አኖርከኝ
(ኦሆ) የምለው የለኝም (ኦሆ) እወድሃለሁኝ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ
እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ