Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መጣሁ ወደ ደጅህ

Metahu Wede Dejeh

2004 · ትራክ 10 · 4:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያልሰጠኸኝ ምን አለ ቀረብኝ የምለው

እንዴት ይሄን ይጠይቅ ከሞት የታደከው

ፍላጐቴ ሞላልኝ ምኞቴም ተሳካ

የሁሉ መደምደሚያ ኢየሱስ ነው ለካ

መጣሁ ወደ ደጅህ ምሥጋና ልሰጥ

መጣሁ ወደ ደጅህ አምልኮ ልሰጥ (፪x)

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ስንፍና አላወራም ክፉ አይወጣም ከአፌ

ሁሌ ያስደንቀኛል ከሞቴ መትረፌ

ይሄ ቀረብኝ ብዬ አላማህም ለሰው

ደም አፍሳሹን ክፉ ሰው ወደህ ከታደከው

መጣሁ ወደ ደጅህ ምሥጋና ልሰጥ

መጣሁ ወደ ደጅህ አምልኮ ልሰጥ (፪x)

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ቆም ብዬ ሳስበው የሆነከውን ለእኔ

ለዘለዓለም ታደከኝ ከዚያ ከኩነኔ

ቀራንዮ ይናገር ጐልጐታ ይመስክር

ለመስቀል ሞት አበቃህ ለእኔ ያለህ ፍቅር

መጣሁ ወደ ደጅህ ምሥጋና ልሰጥ

መጣሁ ወደ ደጅህ አምልኮ ልሰጥ (፪x)

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ሃሌሉያ (፫x) ሃሌ ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ