ሲከፋኝ
Sikefagn
2004 · ትራክ 3 · 5:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘመን ሲከፋ ቀን ሲለዋወጥ
አንተ ግን ያው ነህ የማትለወጥ
ሁሉን ለይቼ አይቼዋለሁ
እንዳንተ ሚሆን የት አገኛለሁ
ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ
ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉም እርቆ ጀርባ ሲሰጠኝ
ተስፋዬ ያልኩት ድንገት ሲከዳኝ
ቀና አደረከኝ እጆቼን ይዘህ
ዳግም አቆምከኝ እንዲህ ሸላልመህ
ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ
ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀን የጣለውን እዩት ይሄን ሰው
ብለው ሲያወሩ መነሻም የለው
ለክፉ ቀን ነህ መኩሪያ መከታ
እያዩኝ ወጣሁ ወደ ከፍታ
ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ
ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ
አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ