ተዋጊ
Tewagi
2004 · ትራክ 4 · 5:43 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው (፪x)
ለሚታመኑበት እህህ ልጆቹን ታዳጊ
በተሰለፈበት እህህ ሁሌ ድል አድራጊ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በገናዬን ስጡኝ አሄ እስኪ ልደርድረው
ከዚህ ከወዳጄ ኤሄ ክፉን ላላቀው
ሌት ተቀን ቢያደባ ጦሩን ቢሰብቅብኝ
እኔ አመልጠዋለሁ አሄሄ አለ ሚዋጋልኝ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው (፪x)
ለሚታመኑበት እህህ ልጆቹን ታዳጊ
በተሰለፈበት እህህ ሁሌ ድል አድራጊ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዳዊት አልፍ ገዳይ ሳዖል ግን ሺህ ብቻ
እያሉ ቢዘፍኑ እርሱ የለው አቻ
ልብህ ቅር አይበለው ክፉ አትመኝለት
የሆነ እንዳሰኘው ቀን እስከወጣለት
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው (፪x)
ለሚታመኑበት እህህ ልጆቹን ታዳጊ
በተሰለፈበት እህህ ሁሌ ድል አድራጊ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሊወግሩኝ ተማማሉ ትላንት የመራኋቸው
ከጨካኙ ጐልያድ ከጡቻው የዳንኳቸው
ነገር ተገለባብጦ ሁሉን ተነሳ በእኔ ላይ
ነገር ግን የሚመለከት ቀን ፈራጅ አለ በሰማይ
በልቤ በቃ አትዘን ይልቅ በርታ በርታ በል
ታያለህ ጌታ በጊዜው ሁሉንም ሲያደርገው ገለል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ ነው (፪x)
ለሚታመኑበት እህህ ልጆቹን ታዳጊ
በተሰለፈበት እህህ ሁሌ ድል አድራጊ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄሄ
እግዚአብሔር ተዋጊ አሄ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ