እወራረዳለሁ
Eweraredalehu
2004 · ትራክ 6 · 6:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እስኪ ልነሳ ልሂድ ልያዘው
ተራራማው ምድር የእኔው እኮ ነው
እርጅና አያውቀኝ እድሜ አይወስነኝ
ዛሬም እንደጥንቱ ጉልበታም ሰው ነኝ
ልቤ አ ይደነግጥ ሁኔታን አይቶ
ለውጥን ያመጣል ጫካ ውስጥ ገብቶ
ልቤ አይደነግጥ ሁኔታን አይቶ
ይመነጥራል ጫካ ውስጥ ገብቶ
አዝማች · Chorus
አልሰማም የጠላትን ዛቻ
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰጥቶኛል ጌታዪ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
አልሰጋም በጠላቴ ዛቻ
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ
ሰጥቶኛል ጌታዬ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
እልፍ ልበል ልሂድ ልተወው
የደከምኩበትን ከተመኘኸው
አልሟገትም የእኔ ነው ብዬ
ፈቀቅ ልበል መብቴን ጥዬ
በፊቴ ወጥቷል የሚዋጋልኝ
በእርሱ ላይ ጥዬ እወጣለሁኝ
የአባቶች አምላክ ላያሳፍረኝ
ርሆቦት ሆኖ በምድር አሰፋኝ
አዝማች · Chorus
አልሰማም የጠላትን ዛቻ
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሰጥቶኛል ጌታዬ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
አልሰጋም በጠላቴ ዛቻ
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ
ሰጥቶኛል ጌታዬ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
እስኪ ልነሳ ልሂድ ልያዘው
ተራራማው ምድር የእኔው እኮ ነው
እርጅና አያውቀኝ እድሜ አይወስነኝ
ዛሬም እንደጥንቱ ጉልበታም ሰው ነኝ
ልቤ አይደነግጥ ሁኔታን አይቶ
ለውጥን ያመጣል ጫካ ውስጥ ገብቶ
ልቤ አይደነግጥ ሁኔታን አይቶ
ይመነጥራል ጫካ ውስጥ ገብቶ
ቁጥር 4 · Verse 4
አልሰማም የጠላትን ዛቻ (አልሰማም)
ቁጥር 5 · Verse 5
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ (እሄዳለሁ)
ሰጥቶኛል ጌታዬ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
አልሰጋም በጠላቴ ዛቻ (እሄዳለሁ)
እሄዳለሁ እስከምድር ዳርቻ
ሰጥቶኛል ጌታዬ ከፋፍቶ
ከፊቴ ማንስ ሊቆም ከቶ
ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው
እርሱ አምላክ ተብሎ ይጠራ
ክርክር አላውቅበትም
ጊዜ አልወስድም ከእናንተ ጋራ
እጮሃለሁ ዛሬ እንደጥንቱ
ይሰማኛል ስለው አቤቱ
መሰዊያው ላይ በእሳት ተገልጦ
ይኸው ይታይ እርሱ ከፍ ብሎ (፪x)
እወራረዳለሁ በአምላኬ በሰማይ ባለው
እወራረዳለሁ የአባቶቼ አምላክ ታማኝ ነው
እወራረዳለሁ ቀኑ አያልቅም/አያልፍም ጌታ ሳይታይ
እወራረዳለሁ አማላኬ ነው በምድር በሰማይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ