በቃ በለው
Beqa Belew
2004 · ትራክ 12 · 4:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጐበስ ቀና ብለህ ያኔ በአምሳልህ የፈጠርከው
አልተገኘም በስፍራው ሆኖ አንተ እንዳስቀመጥከው
በምኞት ተሳበ ወደቀ በጠላት ተረታ
እራሱን በራሱ በደለ መቅሰፍትን አመጣ
የተፍገመገመ እንዳይወድቅ መድኃኒት ላክለት
እንደማይችል አውቅህ እንዲሁ ምህረት አድርግለት
አዝማች · Chorus
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍጥረት ተቀሰፈ አለቀ እንዲሁ በከንቱ
እሮሮና ሃዘን ያሰማል ሁሉም በየቤቱ
ልጆች አዋቂዎች ሳይባል አዛውንቶች ሁሉ
ያለአጋዥ ያለጧሪ ቀርተው ጐዳናውን ሁሉ ሞሉ
ተንከራታቹን ሰው አስበው ልቡን መልስለት
ረሃብ ቸነፈር በሽታውን አንተ አስወግድለት
አዝማች · Chorus
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
ቁጥር 3 · Verse 3
እረ ይቅር በለን ጩኸታችን ይውጣ
የሚያግዝ የለም ወይ እንዲህ ስንቀጣ
ወዴት አቤት እንበል ለማን እንንገረው
ፍጥረት ተቅበዝብዟል አጋዥ እንደሌለው
ከነገሥታት መፍትሄ ጠፍቷል
ከጠቢባን ጥበብ ተሰውሯል
አቅም ያለው ለውጥን የሚያመጣ
አንድም የለም ሚያድነን ከቁጣ
አንተ ግን ሁሉን ቻይ ነህና
የሚሳንህ ምንም የለምና
አግዘው እንጂ ተመልከተው
ይሄ ፍጥረት ካለአንተ ማን አለው
አዝማች · Chorus
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው
በቃ በለው እስኪ ማረው
እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ