Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንኳን ደስ አላችሁ

Enkuan Des Alachehu

2004 · ትራክ 13 · 5:12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የፍቅር አምላክ የሰላም ባለቤት

ቸርነቱን እርሱ ይጨምርበት

በሃዘንም ሆነ በደስታ

አይለያችሁ ይህ ቸሩ ጌታ (፪x)

ፍቅር ይሁን በመሃከላችሁ

ሰላም ይሁን በመሃከላችሁ

ደስታ ይሁን በመሃከላችሁ

እረፍት ይሁን በመሃከላችሁ

እንኳን ደስ አላችሁ (፬x)

ይህንን ውሳኔ በመወሰናችሁ

የፍቅር የሰላም ይሁን ጋብቻችሁ

እኛ ደስ ብሎናል

እንኳን ደስ አላችሁ (፪x)

ፀጋ በረከት ይሙላ በቤታችሁ

ሰላም ጤንነት ሁሌ አይለያችሁ

ምንም አትጡ ጐዶላችሁ ይሙላ

ሁልጊዜ ኑሩ በፍቅር በተድላ (፪x)

ፍቅር ይሁን በመሃከላችሁ

ሰላም ይሁን በመሃከላችሁ

ደስታ ይሁን በመሃከላችሁ

እረፍት ይሁን በመሃከላችሁ

እንኳን ደስ አላችሁ (፬x)

ይህንን ውሳኔ በመወሰናችሁ

የፍቅር የሰላም ይሁን ጋብቻችሁ

እኛ ደስ ብሎናል

እንኳን ደስ አላችሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ