ተመሥገን
Temesgen
2004 · ትራክ 8 · 5:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መውጣቴ መግባቴ በአንተ ተጠብቆ
ከእኔ ጋር እንዳለህ ጠላቴ እንኳን አውቆ
ይሸሸኝ ገመረ በሄድኩበት ስፍራ
ሁሉን አስረገጥከኝ ሆነህ ከእኔ ጋራ
ለአንተ ሲያንህ ነው (፬x)
ደግሜ ደግሜ ስምህን ልባርከው
ያንን ክፉ ዘመን ያለፍኩት በአንተ ነው
እልፍ ቃል ቢነገር አይገልጥህምና
መቅደስህ ገብቼ ልበል ጎንበስ ቀና (፪x)
አዝማች · Chorus
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ተመስገን
ቁጥር 2 · Verse 2
አሳልፈኸኛል ያንን ክፉውን ቀን
ሌላ ቃል የለኝም ልበልህ ተመስገን
አሳልፈኸኛል ያንን ክፉውን ቀን
ሌላ ቃል የለኝም ልበልህ ተመስገን (፪x)
ምክንያት ፈልጌ ላመስግን እንጂ
ሰበብ ፈልጌ ልዘምር እንጂ
ስላልጠፋሁኝ ዛሬም ከአንተ ደጅ (፬x)
ምክንያት ፈልጌ ላመስግን እንጂ
ሰበብ ፈልጌ ልዘምር እንጂ
ስላልጠፋሁኝ ዛሬም ከአንተ ደጅ (፯x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ