በአንተ አልፌ
Bante Alefie
2004 · ትራክ 5 · 6:49 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መቼ ዘነጋሁት የትላንቱን ነገር
ከሞት የመትረፌ አያልቅም ቢነገር
በአደባባይ ልቁም የአረከውን ላውራ
የት እደርስ ነበረ ባልሆን ከአንተ ጋራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትላንትን በአንተ አልፌ
ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ
ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ
ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ እንዳንተ ያለ ለእኔ የለም (፫x)
ጌታ እንዳንተ ያለ ለእኔ የለም (፫x)
የፀሐዩን ብርታት በጥላ ከልለህ
ድቅድቁን ጨለማ በብርሃን ለውጠህ
ቁር ሳያገኘኝ እባቡ ሳይነድፈኝ
አቤት የእኔ ጌታ ከስንቱ ታደከኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትላንትን በአንተ አልፌ
ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ
ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ
ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ትዝ ትዝ ይለኛል ያረክልኝ ሁሉ
ሳልቆጥብ ልናገር ዘመኔን በሙሉ
ጌታ ማዳንህን ለሰው ሳላወራ
አንድም ቀን አያልፍም ስምህን ሳልጠራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትላንትን በአንተ አልፌ
ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ
ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ
ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ