ገለበጠው እንጂ
GelebeTew Enji
2004 · ትራክ 11 · 4:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገለበጠው እንጂ ድንገት ጌታ ደርሶ
ጠላት ሲጠባበቅ ጉድጓድ ለእኔ ምሶ
ነገር ሲፈልገኝ ስፍራ ለማስለቀቅ
በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት
አዝማች · Chorus
ዘምር ዘምር አለኝ
ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እነኛ በፈረሳቸው በሚያልፈው ነገር ታመኑ
በሰረጐቻቸው ብዛት እጅጉን ተገዳደሩ
ግን እንደዋዛ አለፉ ተሰነቃቅለው ወደቁ
የእኔ ግን መተማመኛ አሁንም አለ በክብሩ
አዝማች · Chorus
ዘምር ዘምር አለኝ
ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በንጉሥ ደጃፍ ተጥዬ ሃማ ግልምጫው በርትቶ
ስገድ ሲለኝ አልሰግድም ምንም ቢያይ ተቆጥቶ
እጄን አልሰጥም ለጠላት ክፉ ደግ በእኔ ቢያወራ
ቀን ቆጥሮ አምላኬ ይመጣል ታሪክን በእኔ ሊሰራ
አዝማች · Chorus
ዘምር ዘምር አለኝ
ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጠላት ቢፎክር ቢያቅራራ አዋጅ ቢታወጅ በእኔ ላይ
ከቶ እንዳሰበው አይሆንም አምላኬ እኮ አለ በሰማይ
አዋጅን በአዋጅ ገልብጦ ጌታ መጣና ቀደመው
ነገሩ ተገለበጠ ጠላት ገባ በቆፈረው
ገለበጠው እንጂ ድንገት ጌታ ደርሶ
ጠላት ሲጠባበቅ ጉድጓድ ለእኔ ምሶ
ነገር ሲፈልገኝ ስፍራ ለማስለቀቅ
በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት
አዝማች · Chorus
ዘምር ዘምር አለኝ
ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ