Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንነቃነቅም

Aneneqaneqem

2004 · ትራክ 8 · 5:03 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንነቃነቅም እንቆማለን

መሠረታችን አለት ነው

ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ (፪x)

ማዕበል ቢነሳ ወጀብም ቢመጣ

አይሎ ቢታይም የቆመ ባላንጣ

የሕይወት መሰረት ብርቱ ነው አለቱ

በእርሱ አንጸናለን ብንገባም ከእሳቱ

አንነቃነቅም እንቆማለን

መሠረታችን አለት ነው

ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ (፪x)

የማዕበሉ አዛዥ የሁሉ ፈጣሪ

ብርቱ ነው ኢየሱስ የእኛ ፈጣሪ

እንናገራለን በእርሱ እንደፍራለን

በዘላለም አባት በጸጋው እንቆማለን

አንነቃነቅም እንቆማለን

መሠረታችን አለት ነው

ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ (፪x)

ስማ ዲያብሎስ ሆይ የጨለማው አውራ

እኛ እንደነግጥም ብትነዛ ጉራ

መለከት ብትነፋ በዓለም ብታጮኸው

በዓለት እንቆማለን እንተን በሚፈጨው

አንነቃነቅም እንቆማለን

መሠረታችን አለት ነው

ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ (፪x)

ይሄ ነው ሚስጢሩ የመስቀሉ ጉልበት

የማይነቃነቅ ደም የፈሰሰበት

ክብር ዋጋ ያለው ድንቅ የጌታችን ስም

አያሳፍረንም ሕያው ነው ዘላለም

አንነቃነቅም እንቆማለን

መሠረታችን አለት ነው

ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ